በጣሊያን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ አካሄዱ


በጣሊያን
የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ አካሄዱ=======================================በጣሊያን
የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን የተቀናጀ ዘርፈ ብዙ ጫና ለማውገዝ እና የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት  እንዲሁም የሃገር
መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለውን የአገር ህልውና የማስቀጠል ትግል ለመደገፍ ዛሬ በጣሊያን ሮም ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፉን
በጣሊያን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ያዘጋጁት ሲሆን ሰልፈኞቹ አሸባሪው ህወሃት በአገር እና ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት፣ እድሜ ያልደረሱ ህፃናትን በጦርነት ላይ በማሳተ የሚፈፅሙውን የጦር ወንጀል፣ የሳውዲ አረቢያ መንግስት በህዝቦቻችን ላይ እያደረሰ ያለውን አሳዝኝ ኢሰብዓዊ ድርጊትና የምዕራባውያን አገራትና ተቋማት አገራችን ላይ እያደረጉ ያለውን ያልተገባ ጫና እንዲሁም የሚዲያዎችን የተዛባ ዜና የሚቃወሙ መፎክሮችን አሰምተዋል። በተጨማሪም
ሰልፈኞቹ በዚህ ወቅት ለአገራችን ህልውና ከፍተኛ መስዋትነት እየከፈሉ ላሉ የመከላከያ አባላት፣ የክልሎች ልዩ ሃይል አባላትና ለሌሎች የፀጥታ አካላት ትልቅ እክብሮት እንዳላቸው እና የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስከበር ለሚደርጉት ትግል ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል በተመሳሳይ በሌሎችም አገራት የሚኖሩ ሁሉ የሚደረገውን ድጋፍ በመቀላቀል በአገር አድን ሂደቱ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። በሰልፉ
ኤርትራውያን ወንድሞቻችን የተገኙ ሲሆን አሸባሪው ህውሃት የጦር ወንጀሎችን እየሰራ የቀጠናው ስጋት ሆኖ እያለ በምዕራባውያን ዝም መባሉ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል።
Back to Home

More News ..

በጣሊያን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ አካሄዱ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ከDr. Christian Aimaro እና ፕሮፍ. Dario Peirone ጋር ተወያዩ Read More


በጣሊያንና አካባቢ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ-ኢትዮጵያዊያን ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የበይነ መረብ ውይይት ተካሄደ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ የቱሪን ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንቫይሮመንት ፓርክን ጎበኙ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በጣሊያን ከሚኖሩ የዳያስፖራ ኮሚኒቲ አባላት ጋር በበይነ መረብ ተወያዩ፤ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በጣሊያን ከዳያስፖራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ጋር ተወያዩ፤ Read More


ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ሚላኖ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ፣ Read More


ክብርት አምባሳደር BonelliErede ሃላፊ ጋር ተወያዩ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ከኤርትራ አምባሳደር ከክቡር ፍስሃጽዮን ጴጥሮስ ጋር ተወያዩ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ከኬንያ አምባሳደር ከክብርት ጃክሊና ዩንጋ ጋር ተወያዩ Read More


Read More News...


Subscribe Our News Posts