ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከጣልያን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከጣልያን ውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ከሆኑት ከክብርት ማሪና ሰሬኒ ጋር በጣልያንና በአገራችን መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ስለ አገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲሁም ስለ ህዳሴ ግድብ ተወያዩ፡፡ በውይይቱ በአገራችንና በጣልያን መካከል ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ መልካም ወዳጅነት እንዳለ ያነሱ ሲሆን ይህንን ግኙነት ለማጠናከር በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በአገራችን በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ማለትም በመንግስት በኩል ስለተደረገው የተናጠል ተኩስ አቁም እንዲሁም የሰብሰዊ እርዳታ ለማድረሰ በመንግስት በኩል እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ያብራሩ ሲሆን ምንም እንኳን በመንግስት በኩል የተናጠል ተኩስ አቁም ቢደረግም ጁንታው በኩል ግን ይህንን ያለመቀበል ሁኔታ እንዳለ፣ በክልሉ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደርስ መሰናክል እየሆነ እንዳለ፣ አጎራባች ክልሎችን ማለትም አማራና አፋር ክልልን ለማጥቃት እየሞከረ እንዳለ አንስተው በተለይም ደግሞ ህፃናትን ለውትድርና እየመለመለ ከአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት በሚፃረር መልኩ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የአለም ማህበረሰብ ይህንን እኩይ ተግባር ማውገዝ እንደሚገባውም ገልፀዋል፡፡ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ የአገራችን ፍላጎት ከድህነት መላቀቅና የልማት ፍላጎት እነደሆነና አገራችን በየትኛውም መንገድ የታችኛውን ተፋሰስ አገራት መጉዳት እንደማትፈልግ አስረድተዋል፡፡ ችግሮች በመነጋገርና በውይይት እንደሚፈቱ የገለፁት አምባሳደሯ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረው የሶስትዮሽ ድርድር መፍትሄ ያመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ገለፀዋል፡፡ክብርት ማሪና ሴሪኒ በበኩላቸው በአገራችን በትግራይ ክልል የተከሰተው አለመረጋጋት እንደሚያሳስባቸው ገልፀው ለህብረተቡ እርዳታ ተደራሽ እንዲደረግና ሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጥረት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ የህዳሴን ግድብ በተመለከተ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንደሚፈቱ እም


H.E.
Ambassador Demitu Hambissa Meets Deputy Foreign Minister of Italy H.E. Marina
SereniH.E. Ambassador Demitu Hambissa met H.E. Deputy Foreign Minister of Italy
H.E. Marina Sereni and discussed Bilaterla relations, the current situation in
Ethiopia and the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The two sides highlighted the
long lasting bilateral relation among the two countries and agreed to work
together to further strengthen the relationship.  With regards to the
current situation in Ethiopia, H.E. Ambassaodr Demitu Hambissa explained the
unilateral ceasefire by the government of Ethiopia and the efforts by the
government for the humanitarian assistance to reach to the people of Tigray.The
Ambassador also mentions that even though the government declares the
Unilateral ceasefire, the TPLF junta is not willing to accept the ceasefire
rather the junta continued the reckless acts by hindering humanitarian assistance
not to reach the people, attacking the neighbouring regions like Amhara and
Afar Regions, and to the worst they are recruiting children soldiers in
violation of the International Human Rights Law. The Ambassador calls upon the
international community to condemn these acts of the Junta.In relation to the
Grand Ethiopian Renaissance Dam the Ambassador states that Ethiopia only aspire
development and getting rid of the poverty. the Ambassador underlines that
Ethiopia doesn’t have any intention to cause harm to lower riparian countries
and mentions that the problems will only be solved by peaceful means and the AU
led negotiation will bring a solution that can benefit all the parties.H.E.
Marina Serini on her part expressed that the situation in Tigray is a concern
and calls for the humanitarian assistance to reach the public and for the
protection of Civilians. With regards to the Grand Ethiopian Renaissance Dam,
the Deputy Foreign Minister highlighted that the problem should be solved
peacefully in a way that can benefit all the parties.

ነቱ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡
Back to Home

More News ..

Launch event of the Global Action on Green Development of Special Agricultural-Products: "One Country One Priority Product Read More


በጣሊያንና አካባቢ የምኖሩ ኢትዮጽያዉያንና ትዉልደ እትዮጽያዉያን በኢትዮጽያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የበየነ መረብ ዉይይት አካሄዱ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጣልያን የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ክቡር ሊ ጁንኋ ጋር ተወያዩ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከጣልያን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ Read More


H.E. Amba. Demitu Hambisa Confers with H.E. Adolfo Urso Read More


The Best practices of Ethiopia's School feeding programme presented during the UN Food system pre-summit held on 26-28 July 2021. Read More


The United Nations Food System pre-summit takes its second day in Italy, Rome . Read More


The Ethiopian delegations led by Minister of Agriculture H.E. Oumer Hussein are partaking in the UN Food system pre-summit kicked off on 26 July 2021 in Rome Read More


በጣሊያን ሮም የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ በሮም ከሚኖሩ ከተለያዩ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር በወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ; Read More


ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከክቡር ዶክቶር አብይ አህመድ የተሰጠ መግለጫ Read More


Read More News...

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   48
THIS WEEK:   767
THIS MONTH:   153
THIS YEAR:   26273
TOTAL:    26273
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts