ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከክቡር ዶክቶር አብይ አህመድ የተሰጠ መግለጫ


ለትግራይ ሕዝብ ያለንን ሐሳብ፤ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለንን ቦታ ለመጨረሻ ጊዜ አሳይተናል። ግጭት ላለማባባስ፣ ለሕዝቡ የእርሻ ወቅት ፋታ ለመስጠት እንዲሁም የርዳታ አቅርቦቱ ያለ ሰበብ እንዲከናወን ስንል በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተናጠል የተኩስ አቁም አድርገናል። ሰላም የተወሰነ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ብናውቅም ይህ ግን የመጨረሻ ሰላማዊ ዕድል ነው። ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ እንደሚባለው ጁንታው የሰላም መንገድ ሊዋጥለት አልቻለም። አሁን ባለው ቁመናው ያለ ግጭት ውሎ ማደር አይችልም። ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛለ። የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል። ለሕዝባችን ስንል የከፈልነው ዋጋ ባልገባቸው ደካሞች ምክንያት ውጤት አላመጣም። ጁንታው የኢትዮጵያ ህልውና ቀንደኛ ጠላት መሆኑን ደግሞ እያስመሰከረ ነው። ይሄንንም መላ ሕዝባችንን አስተባብረን እንቀለብሰዋለን። በአንድ በኩል ሰብአዊ ርዳታ እንዲቀላጠፍ እየሠራን በሌላ በኩል የውጭና የውስጥ ጠላቶች ተናበው የከፈቱብንን ጥቃት መክተን እንቀለብሰዋለን።ጁንታው ዋሻ ውስጥ ገብቶ ሕዝቡ በረሐብ ሊያልቅ ነው እያለ ሲያላዝን ነበር። ለሕዝቡ ሲባል ሰብአዊ የተኩስ አቁም ሲደረግ ደግሞ የረሐቡን አጀንዳ ትቶ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም ጀመረ። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ስለ ርዳታና ስለ ረሐብ ሲናገር መቆየቱን ዘንግቶ ጁንታው ሕጻናትን ሲያሰልፍ እንኳን ዝምታን መርጧል። የርዳታ መግቢያ ኮሪደሮችን የግጭት ቦታዎች ሲያደርጋቸው የርዳታ ድርጅቶች አሁንም መንግሥትን ለመውቀስ ይቃጣቸዋል። እነዚህን ሁሉ ከግምት በማስገባት መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ነገር በተገቢው መንገድ ያደርጋል። ሕዝባችን ከሐሰተኛ መረጃዎች እና ከጠላት ፕሮፓጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ አሁንም ለማሳሰብ እንወዳለን። ጁንታውና አጋሮቹ ያላቸው ዐቅም ውሸትን መፈብረክ ብቻ ነውና። የውስጥና የውጭ ኃይሎች ፕሮፓጋንዳቸውን አቀናጅተው ሕዝብን ለመከፋፈል እየሠሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ሕዝባችን እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ እንደ አንድ ሠራዊት ሆኖ ለሀገሩ ህልውና በመቆም፣ የመከላከያ ሠራዊቱን በሁሉም ነገር በመደገፍ፣ የውጪውን ጫና እና የውስጡን ትንኮሳ እንዲመክትና እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን። ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!ሀምሌ 7, 2013 . 
Back to Home

More News ..

Launch event of the Global Action on Green Development of Special Agricultural-Products: "One Country One Priority Product Read More


በጣሊያንና አካባቢ የምኖሩ ኢትዮጽያዉያንና ትዉልደ እትዮጽያዉያን በኢትዮጽያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የበየነ መረብ ዉይይት አካሄዱ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በጣልያን የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ክቡር ሊ ጁንኋ ጋር ተወያዩ Read More


ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከጣልያን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ Read More


H.E. Amba. Demitu Hambisa Confers with H.E. Adolfo Urso Read More


The Best practices of Ethiopia's School feeding programme presented during the UN Food system pre-summit held on 26-28 July 2021. Read More


The United Nations Food System pre-summit takes its second day in Italy, Rome . Read More


The Ethiopian delegations led by Minister of Agriculture H.E. Oumer Hussein are partaking in the UN Food system pre-summit kicked off on 26 July 2021 in Rome Read More


በጣሊያን ሮም የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ በሮም ከሚኖሩ ከተለያዩ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር በወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ; Read More


ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከክቡር ዶክቶር አብይ አህመድ የተሰጠ መግለጫ Read More


Read More News...

VISITOR COUNT
TODAY COUNT:   55
THIS WEEK:   673
THIS MONTH:   2438
THIS YEAR:   20192
TOTAL:    20192
         Services
      * Visa Service
      * Document Authentication
      * For Diplomatic Community
      * For Bussiness Community
      * Government E-Services
         Media
      * Week in the Horn
      * Press Release
      * Speech
      * Articles

Subscribe Our News Posts